
በሀዘናችን ውስጥ የኢየሱስ ማጽናኛ እና ወዳጅነት (The Comfort and Friendship of Jesus in Our Grief)
article
ከአራት ዓመታት በላይ የምወዳት ባለቤቴ ናንሲ ከካንሰር ጋር ተጋፈጠች፣ ብዙ ጥሩ እና ብዙ መጥፎ ሪፖርቶች ነበሩ። በሶስት የቀዶ ጥገና ህክምናዎቿ፣ በሶስት ዙር የጨረር እና የሶስት ዙር ኬሞ በሙሉ በስሜት መለዋወጥ ተጨንቀናል።
ዶክተሩ አሁን ያለው ካንሰር ደረጃ-አራት ካንሰር ነው እናም ወደ ሳምባዋ ተዛምቷል ብሎ የተናገረውን ቀን በደንብ አስታውሳለሁ። በዚያ ምሽት አብረን ጸለይን እና ከዛ ወደ ምድር ቤት ወረድኩ፣ ከሶፋው አጠገብ ተንበርክኬ ፊቴን በእጄ ሸፍኜ አለቀስኩ። ጣልቃ እንዲገባ እየለመንኩት ልቤን ለእግዚአብሔር አፈሰስኩት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7 ‹‹እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።›› እንድናደርግ የሚነግረንን አደረግሁ።